የኤርትራ የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶችና የሰሜን ኣሜሪካ የይበቃል (ይኣክል) እንቅስቃሴ በጋራ፡ የኢትዮጵያ ጠቕላይ ሚኒስተር፡ መስከረም 29/ 2012 ኣዲስ ኣበባ ላይ “ኤርትራን እወክላለሁ” ማለታቸውን እንቃወማለን

2019-10-18 17:25:27 Written by  EPDP Information Office Published in ጽሑፋት ትግርኛ Read 2093 times

ለተከበሩ ዶ/ር ኣብይ ኣሕመድ ዓሊ

የኢትዮጵያ ፈደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስተር

ኣዲስ ኣበባ

የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስተር  

እኛ ስማችን ከታች የተጠቀሰው፡ የኤርትራ የፖለቲካ ድርጅቶች እና፡ ሌሎች በኤርትራና በውጭ ኣገር የምንገጅ ፍትህ ፈላጊና ለፍትህ የምንታገል ኤርትራዊ እንቅስቃሴዎች፡ መስከረም 29/ 2012 ኣዲስ ኣበባ ላይ ብኣንድነት ፓርክ የምርቃ ስነ-ስርዓት ላይ ባሰሙት ንግግር ያለንን ተቃውሞ በግልጽ እንገልጻለን።

ሰባት የኣፍሪቃ ኣገራት መሪዎችና፡ የተላለዩ ዓለም ኣቀፍ ተቋሞች ወኪሎች በተገኙበት፡ ኤርትራን እንደሚወክሉ ስያውጁ እጅጉን ደንግጠናል። በተካሄደው የሰላሳ ዓመታት መራርና ከባድ ዋጋ በተከፈለበት ትግል ለኣላዊነትዋ ያረጋገጠችው ኤርትራ፡ በስነ ስርዓቱ በኣሁኑ ግዜ ኣዲስ ኣበባ ካሉት ሁለት የኤርትራ ኣንበሳድሮች በኣንዳቸው መወከል ነበረባት።

የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስተር

ባሰሙት ንግግር፡ ፕረሲደንት ኢሳይያስ ኣፈወርቅ እንደወከልዎት በግልጽ ጠቅሰዋል። በመቀጠልም በኤርትራና በኢትዮጵያ መሃከል ያለው ግኑኝነት፡ በመወካከል ደረጃ መድረሱን በመጥቀስ በዚ ጉዳይ ላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደስታዎን ገልጸዋል።

የኤርትራ ህዝብ ወድ ዋጋ የከፈለለት ነጻነቱን እጅጉን ያከብራል። እንዲሁም በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የሚመሰረት የኤርትራና የኢትጵያ ግኑኝነት ይደግፋል። እኛ የኤርትራ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና፡ ፍትህ ፈላጊ እንቅስቃሴዎች፡ መጭው የኤርትራ ዕድል ብህዝብዋ እንጂ፡ በኣንባገነኑ የኣስመራው ስርዓት እንደማይወሰን እናምናለን። ከዚህ ኣንጻር ወደሁዋ የማይመለሰውን የኤርትራ ነጻነት እንጠብቃለን። ቀስበቀስ ነጻነታችን እየቦረቦረ ማህበራዊ እሴቶቻችንን እያፈረሰ ያለው ኣንባገነናዊ ስርዓትን እናወግዛለን። በዚህ ኣጋጣሚ ህዝባችን በላዩ እና በለኣላዊነቱ ላይ እየተፈጸመ ባለውን ክህደት ትዕግስቱ ኣየተሟጠጠ መሆኑን እንገልጻለን።

የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስተር

ዓለማችን ኤርትራ ላይ እየታየ ያለው ፖለቲካዊ፡ ማህበራዊ፡ ኤኮኖሚያዊ እና ሰብኣዊ መብት ሁኔታ በሚመለከት ተገቢውን ግንዛቤ ኣላት። በኣሁኑ ግዜ ኤርትራ፡ በህገ-መንግስት ኣትመራም፡ የተመረጠ ኣመራርና መሪ የላትም፡ የሕግ የበላይነትና የሚድያ ነጻነት የላትም፡ በኣጠቃላይ ብኣሁኑ ግዜ በኤርትራ መደበኛ የሚባል ህይወት የለም።

ኣሁን እየታየ ያለው የኤርትራ ህዝብ ወካዩ የመወሰን መብቱ መግፈፍ፡ ለረዥም ግዜ የሚዘልቅ ኣይደለም። እስከዛ ማነኛውም ኤርትራዊ ያልሆነ ወገን በኤርትራ ጉዳይ ላይ የመናገር መብትም ሞራልም የለውም።

ኣሁን ያለው የህዝባችን ኣሰቃቂ ህይወት ለመቀየር እያደረግነው ያለነው ትግል፡ ነገ ታሪክ እንደሚሆን እርግጠኞች ነን። ብህዝባችን ምኞትና ፍላጐት ላይ የተመሰረተ ሰላም እንደሚመጣም ኣንጠራጠርም። ዛሬ ከኤርትራ ህዝብ ጋር መወገን፡ ለወደፊቱ በኤርትራን በኢትዮጵያ መሃከል ወደ ሚመሰረተው ኣስተማማኝ ግኑኝነት የሚወስድ ትክክለኛ መንገድ ነው። በኣከባብያችን ኣስተማማኝ ሰላም እንዲረጋገጥ የሚፈልጉ ወገኖች ከጨቋኞችና ኣፍራሾት ጋር መዛመድ የለባቸውም እንላለን።

ኣገራችን ኣስቸጋሪ ሁኔታ ባለችበት በኣሁኑ ግዜ፡ የኢትዮጵያ መንግስት በሺዎች ለሚቆጠሩ ኤርትራውያን መጠለያ በመስጠቱና ሌሎች ድጋፎች በማድረጉ በድጋሚ እናመሰግነዋለን። የሰላም የኖቤል ሽልማት ኣሸናፊ በሆኑበት ኣጋጣሚ፡ በኤርትራ ላይ ባለዎት ኣመለካከት ጥንቃቄ የተሞላው ማስተካከያ እንድያደርጉ፡ ከኤርትራ ህዝብ ጋር ያለዎት ግኑኝነት እንዲያጐለብቱና በኣከባብያችን በሃገሮች መሃከል ተቋማዊና ቀጣይ ሰላም ለማረጋገጥ እንዲሰሩ ጥርያችን እናቀርባለን።

ኣክባሪዎ

የኤርትራ ኣገራዊ ሸንጎ ለዲሞክራስያዊ ለውጥ (ኤኣዲለ)

የኤርትራ ዲሞክራስያዊ ህዝባዊ ፓርቲ (ኤዲህፓ)

የኤርትራውያን ኣንድነት ለፍትህ (ኤኣፍ)

የሰሜን ኣሜሪካ የይበቃል (ይኣክል) ሸንጎ

ጥቅምት 4/ 2012 ( 15/10/2019)